0% found this document useful (0 votes)
183 views92 pages

G2 Text Final Edited Hpe

HPE

Uploaded by

maranatha1303
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
0% found this document useful (0 votes)
183 views92 pages

G2 Text Final Edited Hpe

HPE

Uploaded by

maranatha1303
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd

+

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት

የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ

ሁለተኛ ክፍል

0
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት

የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ

ሁለተኛ ክፍል

አዘጋጆች፡-

ዳዊት ሽፈራው

ሰለሞን ወርቁ

ያሬድ ገዛኸኝ

አርታኢዎችና ገምጋሚዎች
ተስፋዬ አቤ

ወንድአለ ሥጦቴ

አዶንያስ ገ/ሥላሴ

ውብዓለም በየነ

አስተባባሪ
ጌታቸዉ ታለማ

አቀማመጥ እና ስዕል
እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
© በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ አዲስ

አበባ 2015 ዓ.ም

ምስጋና

ይህን የትምህርት መፅሐፍ ዝግጅት ተጀምሮ በውጤት


እንዲጠናቀቅ፣ የካበተ ልምዳቸውን በማካፈል፣ በፓናል ውይይት
ሃሳብ በማፍለቅና በማቅረብ፣ በከተማችን በሚያስተምሩ መምህራን
እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ አስፈላጊውን በጀት በማስፈቀድ እንዲሁም
በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመራ በማድረጋቸው ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ
የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የላቀ ምስጋና
ይገባቸዋል።

ለሥራችን መሳካት ሁል ጊዜ አብረውን በመሆን፣ በሚያጋጥሙ ችግሮች


መፍትሄ በመስጠት፣ የአፈጻጸም ሂደቱን በመከታተል፣ በመገምገም
እንዲሁም የዝግጅቱ ስራ ቁልፍ ስራ መሆኑን ተረድተው ትኩረት
በመስጠት ከጎናችን ለነበሩ የትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት
የስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ፣
የትምህርት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ
የመምህራን ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ፣
የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ፣ የትምህርት ቢሮ
ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ፣ የቴክኒክ አማካሪ አቶ ደስታ መርሻ
ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባቸዋል።

በመጨረሻም መጽሐፉ ተጀምሮ እስከሚ ጠናቀቅ ድረስ የትምህርት ቤት


ርዕሳነ መምህራን ለስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት አዘጋጅ መምህራንን
ስለላካችሁልንና የሞራል ድጋፍ ስላደረጋችሁ ምስጋናችንን
እናቀርባለን።
ማውጫ
መግቢያ
ምዕራፍ አንድ
....................................................
መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት 1
1.1.አቅጣጫን በመቀየር በፍጥነት የመንቀሳቀስ ክህሎት ............2
1.2.ቅንጅታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት ...................................................6
1.3.በቦታ ላይ በመሆን የሚሰሩ የእንቅስቃሴ ቅንጅታዊ ክህሎት
..................................................................................... 9
ምዕራፍ ሁለት ........................................................................... 15
ተከታታይነት ያለው የእንቅስቃሴ ክህሎት
2.1.ተከታታይነት ወይም ቀጣይነት ያለዉ የእንቅስቃሴ ክህሎት
....................................................................................16
2.2.የሚሻሻል ወይም የሚለወጥ ተከታታይነት ያለው
የእንቅስቃሴ ክህሎት .........................................................18
ምዕራፍ ሦስት
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ በማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት... 27
3.1. ራስን የመምራትና የመገንዘብ ክህሎትን የሚያዳብር
የሰዉነት እንቅስቅሴ ..........................................................28
3.2. ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያዳብሩ የአካል እንቅስቃሴ
ክህሎቶች ........................... ............................................31
3.3. የአካል እንቅስቃሴ ኋላፊነት ለሚሰማው ውሳኔ አሰጣጥ...36
ምዕራፍ አራት
የጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ...............................................42
4.1. የልብና የአተነፋፈስ ብርታት እንቅስቃሴ..................................43
4.2. የጡንቻ ብርታት እንቅስቃሴ ......................................48
4.3. መዘርጋትና መታጠፍ /Flexibility/.............................50
4.4. ቅልጥፍና..........................................................53

I
ምዕራፍ አምስት

ጅምናስቲክ. ..............................................................................61

5.1.ቀላል የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች ...............................62

5.2. ድብልቅ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች .........................68


ምዕራፍ ስድስት

የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች .......................74

6.1. ተማሪዎች በሚኖሩበት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ


የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች ...................................75

6.2. ተማሪዎች በሚኖሩበት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ


የተወሰኑ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች .......................78
የቁልፍ ቃላት ፍቺ .................................................................... 83

ዋቢ መጽሀፍት ......................................................................... 84

II
መግቢያ
ተማሪዎች በዚህ የክፍል ደረጃ በጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ

ትምህርት በጨዋታ መልክ በመማር እዉቀታቸውንና

ክህሎታቸውን ያዳብራሉ፡፡ በተጨማሪም በአኗኗር ዘይቤያቸው

ውስጥ ደስተኛ ሆነው በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ ጤናማ

ህይወት እንዲኖራቸው እና ኋላፊነታቸውን የሚወጡ ዜጎች

ለመፍጠር አስተዋፅኦ አለው፡፡ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ

ትምህርት የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ߹ ጥልቅ የሆነ የአስተሳሰብ

ልህቀት߹ ውሳኔ የመስጠት አቅም እንዲሁም ችግሮችን የመፍታት

ብቃታቸው ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት

ከዚህ በፊት በነበረው የተቀናጀ የትምህርት ስርዓት በማውጣት

እራሱን ችሎ እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም ትምህርት

ከተማሪዎች ነባራዊ ህይወት ጋር በመቀናጀቱ በበቂ ሁኔታ

ትምህርቱን ለመማርና ዓላማውን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ

ይኖረዋል፡፡

III
1 ምዕራፍ አንድ

መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት


መግቢያ
መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት ሃይልን በመጠቀም ሁሉንም

የአካል ክፍል የሚያዳብሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም የመራመድ፣

የመሮጥ፣ የመዝለል እና የመወርወር እንቅስቃሴዎችን ያካትታል፡፡

እነዚህን አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለማከናወን ኃይልን ከምንመገበው

ምግብ እናገኛለን፡፡
በዚህ ምዕራፍ የሚካተቱ የትምህርት ይዘቶች የመንቀሳቀስ ክህሎት
߹ በቦታ ላይ የመንቀሳቀስ ክህሎት እና በብቃት የመስራት ክህሎት
ናቸው፡፡

የመማር ዉጤቶች፡ ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በግማሽ/ክብ ቅርፅ ለየብቻ በፍጥነት መንቀሳቀስን ሰርታችሁ


ታሳያላችሁ߹
• በአንድ ቦታ ላይ በመሆን በዕቃዎች ላይ የመንቀሳቀስ ቅደም
ተከተልን ሰርታችሁ ታሳያላችሁ߹
• ዕድሜን ማዕከል ያደረገና ሁለት ትንንሽ
2 ኳሶችን በመጠቀም ከወገብ
በላይ ያለውን የሰዉነት ክፍል ታንቀሳቅሳላችሁ߹
• የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ፈጥራችሁ ታሳያላችሁ߹

1
• የሰዉነት ክፍሎችን በመጠቀም ከጓደኞቻችሁ ጋር የተለያዩ የሰዉነት
ቅርፆችን ትሰራላችሁ::

1.1. የመንቀሳቀስ ክህሎት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• በቦታ ላይ በመሆንና በመንቀሳቀስ ዕድሜን ማዕከል ያደረገ ቅንጅታዊ


እንቅስቃሴዎችን ትሰራላችሁ߹
• በቡድን በመቀባበል እንቅስቃሴዎችን ትሰራላችሁ߹
• ከጓደኞቻችሁ ጋር አዎንታዊ በሆነ ግንኙነት ብቃታችሁን ሰርታችሁ
ታሳያላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

የመንቀሳቀስ ክህሎት ምን ማለት ነው?


የመንቀሳቀስ ክህሎት ማለት ወደፊትና ወደ ኋላ߹ ወደ ቀኝና ወደ
ግራ እና ወደ ጎን መንሸራተትን ያካትታል፡፡ ይህን በማከናወን
ተማሪዎች ፍጥነታችሁን߹ ቅልጥፍናችሁን߹ ሚዛን መጠበቅ
እንዲሁም አጠቃላይ ክህሎታችሁና ጤንነታችሁን ታሻሽላላችሁ፡፡

ተግባር 1:-ሰለሜ ሰለሜ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በተርታ ተሰልፋችሁ እርስ በእርስ መያያዝ፡፡
• ከፊት ለፊት አንድ ተማሪ የተጠቀለለ ጨርቅ /ፎጣ/
ለመግረፊያ መያዝ፣

2
• ከኋላ ያላችሁ ተማሪዎች ከፊት ያለውን/ችውን ተከትላችሁ
አቅጣጫችሁን በመቀያየር /ዚግዛግ/ በመሮጥ ሰለሜ ሰለሜ
ኦያ ሰለሜ እያላችሁ መከተል፣
• ከፊት የሚመራውን /ምትመራውን/ በመቀያየር
እንቅስቃሴውን መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 1 ፡- እርስ በርስ4 ተያይዘው ዚግዛግ ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ

ተግባር 2፡- ደርሶ መልስ ሩጫ


የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች በሁለት ተርታ መሰለፍ ከሁለቱም ተርታ ፊት ለፊት
መነሻና መድረሻ የሚያገለግሉ ኳሶች /ቅምብቢቶች/ በ5 ሜትር
ርቀት ላይ ማስቀመጥ፣
• ከሁለቱም ተርታ አንዳንድ ተማሪዎች ከመነሻችሁ በመነሳት
ወደፊት እኩል መሮጥ፣
• የመድረሻውን ኳስ /ቅምብቢት/ በውጪ በመዞር በሩጫ
ተመልሳችሁ ከኋላ መሰለፍ፣
• በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴውን መቀጠል߹
• ቀድሞ የጨረሰ ተረታ አሸናፊ ይሆናል߹

3
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 2፡- በተርታ ተሰልፈው ከቅምብቢት ፊት ለፊት


አንድ ተማሪ ቅምብቢቱን ሲዞር የሚያሳይ

ተግባር 3፡- እግርና እጅ መክፈት መግጠም (Jump Jack)

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በረድፍ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሰለፍ፣
• እግራችሁን ገጥማችሁ እጃችሁን በጎን ታፋችሁ ላይ ማድረግ፣
• ቀለል ባለ እንቅስቃሴ እግራችሁን ከመሬት በመልቀቅ ወደ
ግራና ወደ ቀኝ መክፈት፣
• እንዲሁ እጃችሁን ወደ ጎን በመዘርጋትና በጭንቅላታችሁ
በላይ በማሳለፍ በሁለት እጃችሁ ማጨብጨብ፣
• ከዚያም እግራችሁን በመግጠም መሬት ላይ በማረፍ
እጃችሁን ከተዘረጋበት በመመለስ በጎን ታፋችሁ ላይ
ማድረግ፣
• በዚህ ሁኔታ ከዝግታ ወደ ፍጥነት ድግግሞሹን መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

4
ስዕል 3 እግርና እጅ መክፈት መግጠም

ተግባር 4:- ወደ ፊትና ወደ ኋላ መዝለል

የአሰራር ቅደም ተከተል

በመጫወቻ ሜዳ ላይ ከተዘጋጀው ክብ ውጭ ርቀትን ጠብቆ


ዙሪያውን መቆምና የመምህር ትዕዛዝ መጠበቅ፣

• አንድ ሲባል ሁለት እግራችሁን ገጥማችሁ ወደ ክቡ ዘሎ


መግባት፣
• ሁለት ሲባል ከክቡ ዘሎ መውጣት፣
• የተሳሳተ ተማሪ ከጨዋታ ውጭ ይሆናል፣
• በዚህ ሁኔታ ጨዋታው ይቀጥላል መጨረሻ የቀረ አሸናፊ
ይሆናል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

5
የግምገማ ጥያቄዎች

1. የመንቀሳቀስ ክህሎት ምን ጠቀሜታ አለው?


2. ለእንቅስቃሴ የምንጠቀምባቸውን አቅጣጫዎች ዘርዝሩ፡፡

1.2.በቦታ ላይ በመሆን የመንቀሳቀስ ክህሎት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• በቅደም ተከተል በመንቀሳቀስና በቦታ ላይ በመሆን ከአንደኛው ወደ


ሌላኛው እንቅስቃሴ በጥንቃቄ የማለፍን ክህሎት ሰርታችሁ
ታሳያላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

በቦታ በመሆን ለምን እንቅስቃሴዎችን እንሰራለን?

ተማሪዎች ቦታ ላይ በመሆን የተለያዩ የአካል ክፍሎቻችሁን በተለይ


እጃችሁን߹ እግራችሁን እና ጭናችሁን በመጠቀም የተለያዩ አካላዊ

6
እንቅስቃሴዎች የምታከናውኑበት ክህሎት ነው፡፡ ይህ አካላዊ
እንቅስቃሴ በቂ ቦታ በሌለበት ስፍራ እንዴት ተቀናጅቶ መስራት
እንደሚቻል ያሳያል፡፡

ተግባር 1፡- ኳስ በቅርጫት ማስገባት

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በአራት ተርታ ከጎድጓዳ ሳህኖች ፊት ለፊት መሰለፍ߹
• ከ3-5 የሚደርሱ ትናንሽ ኳሶች ከሳህኖቹ ጀርባ ይቀመጣሉ߹
• ከየሰልፉ አንድ አንድ ተማሪዎች መሬት ላይ በመቀመጥ
በሁለት እግራችሁ ኳስ እያነሳችሁ 9 ሳህን ውስጥ ተራ በተራ
መክተት߹
• ከዚያም ከየቡድኑ ቀድመው ለጨረሱ ተማሪዎች
ማጨብጨብ߹
• ተግባሩን ሁላችሁም ተማሪዎች ስሩት߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 5 ፡- ተቀምጠው ኳስ ቅርጫት ማስገባት

7
ተግባር 2፡- መቀመጫ በእግር መምታት (Buttock Kick)

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በቦታችሁ በመሆን እግራችሁን በትከሻ ስፋት መክፈት፤

• የእጃችሁን መዳፍ መቀመጫችሁ ላይ ማድረግ፣


• እግራችሁን ወደ ኋላ ማጠፍ፣
• ከዚያም በተረከዛችሁ የእጃችሁን መዳፍ በመምታት
በድግግሞሽ መስራት߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 6፡- መቀመጫን በ ሁለት እግር እያፈራረቁ መምታት

የግምገማ ጥያቄዎች

1. በቦታ ላይ ከምናከናውናቸው ጨዋታዎች ሁለቱን ጥቀሱ፡፡

2. የታችኛው የሰዉነት ክፍሎችን ግለፁ፡፡

8
1.3. በብቃት የመስራት ክህሎት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ


በኋላ፡-
• ከሌሎች ጋር በትብብር መስራትን ታሳያላችሁ߹
• የቅንጅታዊ እንቅስቃሴዎችን ክህሎት ሰርታችሁ ታሳያላችሁ߹
• ከሌሎች ጋር በትብብር ትሰራላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

የማስተማሪያ መሣሪያ ምን ጥቅም አለው?


በብቃት የመስራት ክህሎት ማለት አንድን ተግባር ወይም እንቅስቃሴ

በቀላሉ መስራት ነው፡፡ በመሆኑም የተለያዩ ማስተማሪያ መሳሪያዎችን

በተግባር በመሞከርና በመጠቀም ትምህርትን ተጨባጭ ማድረግ

ይቻላል፡፡ ይህም ትምህርትን የበለጠ ግልፅ ለማድረግና በቀላሉ

ለመረዳት ከፍተኛ እገዛ አለው፡፡

ተግባር 1፡- ኳስ በእግር መምታት

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በተርታ በመሰለፍ አንድ ተማሪ መለየት እና ከ3 ሜትር
ርቀት ላይ ቆሞ/ማ የላስቲክ ኳስ እንዲያቀብል/ድታቀብል
ማድረግ፣
• ተማሪዎች የተመታላችሁን በተራ በውስጥና በውጭ
እግራችሁ መመለስ፣
• ኳስ አቀባይ በመቀየር በድግግሞሽ መስራት߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

9
ስዕል 7፡- ኳስ በውጪና በውስጥ እግር መምታት
ተግባር 2;- የመውጣት መውረድ እንቅስቃሴ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በረድፍ ፍራሹ ፊት ለፊት እግራችሁን ከፈት አድርጋችሁ
መቆም፡፡
• ቀኝ እግራችሁን ፍራሽ ላይ ማውጣት፣
• ከዚያ ግራ እግራችሁን /መሬት የነበረውን/ ፍራሽ ላይ
ማውጣት፣
• መጀመሪያ ፍራሽ ላይ የወጣውን የቀኝ እግር ወደ ነበረበት
መመለስ፣
• በተመሳሳይ ግራ እግርን ወደ ነበረበት መመለስ፣
• ይህን በድግግሞሽ መስራት߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 8፡- ፍራሽ ላይ መውጣትና መውረድ


10
ተግባር 3፡- የእግር ኳስ ቅብብሎሽ ጨዋታ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በሁለት ተርታ ፊት ለፊት በ5 ሜትር ርቀት መሰለፍ፡፡
እንዲሁ ከፊት ለፊታችሁ አማካይ ቦታ ላይ በ1ሜትር ስፋት ሁለት
ቅምብቢቶች ይቀመጣሉ፡፡
• በተራ በቅምብቢቶች መካከል ለጓደኞቻችሁ ኳስ ማቀበል፣
• ተግባሩን ከሰራችሁ በኋላ ወደ ኋላ በመመለስ መሰለፍ፣
• ድግግሞሹን በዚህ ሁኔታ መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 9፡- የእግር ኳስ ቅብብሎሽ ጨዋታ

ተግባር 4፡- ዒላማ መምታት

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በሁለት ረድፍ 5 ሜትር ርቀት ላይ ኢላማ ፊት ለፊት

11
መሰለፍ፣
• በቀኝና በግራ እጃችሁ ቀላል ኳሶችን ኢላማው ላይ
መወርወር፣
• ሁላችሁም በየተራ በመወርወር ወደ ኋላ ሄዳችሁ መሰለፍ፣
• በዚህ ሁኔታ ድግግሞሹን መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 10፡- በኳስ ዒላማ መምታት

የግምገማ ጥያቄዎች

1. ተማሪዎች የማስተማሪያ መሳሪያዎችን


እንዴት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ ?
2. በብቃት የመስራት ክህሎት ምን ማለት ነው ?

12
የምዕራፉ ማጠቃለያ

ይህ ምዕራፍ ተማሪዎች በቀላሉ መሰረታዊ እንቅስቃሴዎችን እንድታስተውሉና


እንድትለማመዱ የሚያደርግ ሲሆን ከትምህርቱም በዕድሜ ደረጃችሁ የአካል
ብቃታችሁን߹
ክህሎታችሁን እንዲሁም ቅልጥፍናችሁን እንድታዳብሩ የሚረዱ

አካላዊ እንቅስቃሴዎችን አከናውናቸኃል፡፡

13
የማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት በማለት


መልሱ፡፡

1. መራመድና መሮጥ መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት


ነው፡፡

2. አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ኃይል ያስፈልገናል፡፡

3. የመንቀሳቀስ ክህሎት ወደ ጎን መንሸራተትን ያካትታል፡፡

4. አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በቂ ቦታ ከሌለ መስራት

አይቻልም፡፡
19
5. የማስተማሪያ መሳሪያ ትምህርትን ተጨባጭ ለማድረግ

ይጠቅማል፡፡

ለ. አጭር መልስ ስጡ፡፡

6. እርስ በእርስ ተያይዘን ዚግዛግ እየሮጥን የምንጫወተው

ጨዋታ ምን ይላል?

7. ኳስ በእግር ስንቀባበል በየትኛው የእግር ክፍል ልንመልስ

እንችላለን?

14
2 ምዕራፍ ሁለት

ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች

መግቢያ
ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች ማለት ያለማቋረጥ

የሚከናወኑ አጠቃላይ የሰዉነት ክፍሎችን በመጠቀም ከቀላል ወደ

ከባድ እና ቆይታውን በጠበቀ መልኩ የሚሰሩ ተግባራት

ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች መደበኛ߹ ፍሰት ያለውና ዕድገት ባለው

የፍሰት ምት ልናከናውነው እንችላለን፡፡ ይህን ተግባር ከተለያዩ ያለ

ሙዚቃ እና በሙዚቃ ምት በማቀናጀት የሰዉነት ክፍሎቻችሁን

ልታዳብሩ ትችላላችሁ፡፡

በዚህ ምዕራፍ የሚካተቱ የትምህርት ይዘቶች መደበኛ የሆነ የምት

ድግግሞሽ߹ ፍሰት ያለው የምት አማራጭና ዕድገት ያለው ምት ደረጃ

ናቸው፡፡

15
የመማር ዉጤቶች፡ ተማሪዎች ይህንን
21
ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ተከታታይነት ያለው እንቅስቃሴ የመስራት ችሎታን ታዳብራላችሁ߹


• ደረጃውን እየጨመረ የሚሄድ ተከታታይነት ያለው እንቅስቃሴን
በመስራት ታሳያላችሁ߹
• በቀላሉ በግላችሁ የፈጠራችሁትን ተከታታይነት ያለው እንቅስቃሴ
ታሳያላችሁ߹
• በምት የተቀነባበረ እንቅስቃሴ ጥበብን ታደንቃላችሁ߹
• ስህተት የሆነ እንቅስቃሴና ምትን ለማረም ከጓደኞቻችሁ ጋር
ትግባባላችሁ߹

2.1. መደበኛ የሆነ የምት ድግግሞሽ


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ
በኋላ፡-

• በመምህር መሪነት ተከታታይነት ያለው መደበኛ እንቅስቃሴን


ትሰራላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

መደበኛ የሆነ የምት ድግግሞሽ ምንማለት ነው?


መደበኛ የሆነ የምት ድግግሞሽ ማለት ተከታታይነት ያለው
በተመሳሳይ ቦታና ጊዜ ከአንዱ ተግባር ወደ ሌላኛው ተግባር
የሚሸጋገር ነው፡፡ ተግባሩ በሚከናወንበት ጊዜ ቅደም ተከተልን
በያዘ መልኩ የእንቅስቃሴው ጫና ከቀላል ወደ ከባድ የሚሄድና
ቆይታውም በጊዜ ሂደት የሚሻሻል ነው፡፡

ተግባር 1፡- አረንጓዴ߹ አረንጓዴ

የአሰራር ቅደም ተከተል

16
ተማሪዎች በሜዳ ላይ ክብ ሰርታችሁ ቀለል ያለ የሶምሶማ ሩጫ
ማድረግ፣
• አረንጓዴ߹ አረንጓዴ ሲባል እንቅስቃሴውን በሶምሶማ
መቀጠል፣
• ቢጫ ሲባል ባላችሁበት ቦታ ቁጭ ማለት፣
• ቀይ ሲባል ባላችሁበት ቦታ መቆም፡፡ በዚህ ሂደት ጨዋታውን
መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 11፡- አረንጓዴ߹አረንጓዴ ጨዋታ

ተግባር 2፡- ወደ ጎን መታጠፍ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በረድፍ በመሰለፍ እግራችሁን በትከሻ ስፋት ከፍታችሁ
መቆም፣
• ሁለት እጅ ወገብ ላይ ማድረግ፣
• ከወገብ ወደ ቀኝ በማዘንበል ቀኝ እጅ ወገብ ላይ ማድረግና
ግራ እጅ ወደ ላይ በመዘርጋት የሰዉነት እንቅስቃሴን
ማስከተል፣
ጨርቅ ይዞ የሚያሳይ
17
• ከወገብ ወደ ግራ በማዘንበል ግራ እጅ ወገብ ላይ ማድረግና
ቀኝ እጅ ወደ ላይ በመዘርጋት የሰዉነት እንቅስቃሴን
ማስከተል፣
• ይህን ተግባር በድግግሞሽ መስራት፣
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 12፡- ወደ ጎን መታጠፍ

የግምገማ ጥያቄዎች

1. መደበኛ የሆነ የምት ድግግሞሽ የት ሊሰራ ይችላል?


2. በአረንጓዴ߹ አረንጓዴ ጨዋታ ጊዜ ቀይ ሲባል ምን
እናደርጋለን?
2.2. ፍሰት ያለው የምት አማራጭ

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡


ተማሪዎች ይህን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-
• ተከታታይነት ያለው እንቅስቃሴ25 ምትን ያለ ሙዚቃ በመምህር

መሪነት ተግባራዊ ታደርጋላችሁ߹

18
የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ
ፍሰት ያለው የምት አማራጭ ማለት ምን ማለት ነው?
ፍሰት ያለው የምት አማራጭ መጀመሪያ ከነበረው እየጨመረ የሚሄድ ወይም
ከአንዱ ወደ ሌላው ተያያዥነት ባለው መልኩ የሚለወጥ፤ የሚተካካ እንቅስቃሴ
ነው፡፡ በሂደት ከግልፅ ወደ ውስብስብ እያደገ የሚሄድ አካላዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡
ይህ እንቅስቃሴ በመደበኛነት ሲሰራ የአካል ብቃትን ለማሻሻል ከፍተኛ
አስተዋፅዖ አለው፡፡

ተግባር 1፡- የቁጥር ጨዋታ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በሁለት ረድፍ ፊት ለፊት በ1 ሜትር ስፋት
ትቀመጣላችሁ በመኃከላችሁ ለሁለት ተማሪ አንድ ኳስ
ይቀመጣል፣
• አንድ ሲባል ጭንቅላታችሁን መያዝ፣
• ሁለት ሲባል ትከሻችሁ ላይ እጆቻችሁን ማድረግ፣
• ሦስት ሲባል በሁለት እጆቻችሁ ወገባችሁን መያዝ፣
• አራት ሲባል ጉልበታችሁን መንካት፣
• አምስት ሲባል ኳስን ከተቀመጠበት ማንሳት፤ ከዚያም
በድግግሞሽ መስራት߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 13፡- የቁጥር ጨዋታ

19
ተግባር 2፡- ጉልበት ማንሳት /knee -drive/

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በረድፍ በመሰለፍ እግራችሁን በትከሻ ስፋት ከፍታችሁ


መቆም፣
• መጀመሪያ በቦታ ቀላል ሶምሶማ መስራት፣

• በመቀጠል ሁለት እጃችሁን ከላይ ወደ ታች በማውረድ፣

በተቃራኒው እግራችሁን ተራ በተራ ወደ ላይ በማጠፍ

ጉልበታችሁን ማስነካት፣

• ይህን ተግባር በድግግሞሽ መስራት߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 14፡- ጉልበት ማንሳት

20
የግምገማ ጥያቄዎች

1. ፍሰት ያለው የምት አማራጭ መስራት ምን ጥቅም


አለው?
2. ፍሰት ያለው የምት አማራጭ እንዴት ሊገለፅ ይችላል?

2.3. ዕድገት ያለው የምት ደረጃ

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• ዕድገት ያለው ተከታታይ እንቅስቃሴ በሙዚቃ ታግዛችሁ

ታሳያላችሁ ߹

• አዎንታዊ በሆነ መልኩ ከጓደኞቻችሁ ጋር የመገናኘት ችሎታን

ታሳያላችሁ ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

ዕድገት ያለው ምት ደረጃ ምን ማለት ነው?

ዕድገት ያለው ምት ደረጃ ማለት ተከታታይ የሆነና ያለማቋረጥ

የሚከናወን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ ሶስቱን ተከታታይነት ያላቸው

እንቅስቃሴዎችን አዋህደን ልናከናውን እንችላለን፡፡ እንዲሁም


ተያያዥነት ባለው መልኩ የሚለወጥ ከግልፅ ወደ ውስብስብ

እያደገ የሚሄድ አካላዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በአግባቡ


ሲሰራ የተሻለ ጤንነት߹ አካል ብቃትና የተስተካከለ ቁመና ይኖረናል፡፡

21
ተግባር 1፡- ዑደታዊ ጨዋታ/cerciut/

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በሁለት ተርታ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሰለፍ፤ ከፊት

ለፊታችሁ በአራት ሜትር ርቀት ሦስት ቅምብቢቶች /ኳሶች/

ይቀመጣሉ፡፡
• የመጀመሪያው ቅምብቢት /ኳስ/ ጋር በርምጃ መድረስና

ባላችሁበት ቦታ መሮጥ፣

• ሁለተኛው ቅምብቢት /ኳስ/ ጋር መድረስና እጃችሁን

መቀመጫቹ ላይ በማድረግ እግራችሁን ወደ ኋላ አጥፋችሁ

በተረከዛችሁ የእጃችሁን መዳፍ መምታት፣

• ሦስተኛው ቅምብቢት /ኳስ/ ጋር መድረስና በእግራችሁ

መሬት በመልቀቅ ወደ ጎን መክፈት እንዲሁ እጃችሁን

በመዘርጋት ከጭንቅላታችሁ በላይ በማሳለፍ ማጨብጨብ፣


• ከአንዱ ቅምብቢት /ኳስ/ ወደ ሌላኛው በርምጃ መሄድና

ስትጨርሱ ከኋላ መሰለፍ߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

22
ተግባር 2፡- አራቱ ߵመߴ በቁጢጥ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በረድፍ በመሰለፍ እግራችሁን በትከሻ ስፋት ከፍታችሁ

መቆም፣
• እጅን በሰዉነት ትክክል ወደ ታች አድርጎ እግርን ገጥሞ
መቆም߹
• እጅን ወደ ኋላ በመደገፍ በእግር ጣት ቁጢጥ ማለት፣
• ከወገብ ቀጥ ብሎ እጅን ጭን ላይ በማድረግ በጉልበት
መንበርከክ፣
• ከወገብ ቀጥ በማለት በመቀመጫችሁ መሬት ላይ

እግራችሁን ዘርግታችሁ በመቀመጥ ሁለት እጃችሁን ጭናችሁ

ላይ ማድረግ፣
• ሙሉ በሙሉ በጀርባችሁ በመተኛት ሁለት እጃችሁን

ጭናችሁ ላይ ማድረግ፣

• ከዚያም ሂደቱን በተደጋጋሚ መስራት߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

23
ስዕል 15፡- ከላይ መቆም ፣ መምበርከክና መተኛት

የግምገማ ጥያቄዎች

1. ዕድገት ያለው ምት ደረጃ ወደ የት ይለወጣል?

2.ዕድገት ያለው ምት ደረጃ ምን ጥቅም አለው?

24
የምዕራፉ ማጠቃለያ

ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች በሙዚቃና ያለ ሙዚቃ

በማቀናጀት የሚሰሩ ተግባራት ናቸው፡፡ እነዚህም መደበኛ የሆነ የምት

ድግግሞሽ߹ ፍሰት ያለው ምት አማራጭ እና ዕድገት ያለው ምት ደረጃ

ውስጥ የተካተቱ እንቅስቃሴዎችን ይይዛል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ

ተከታታይነት ያለው በተመሳሳይ ቦታና ጊዜ ከአንዱ ተግባር ወደ

ሌላኛው ተግባር የሚሸጋገር߹ መጀመሪያ ከነበረው እየጨመረ

የሚሄድ ወይም ከአንዱ ወደ ሌላው ተያያዥነት ባለው መልኩ

የሚለወጥ እና የሚተካካ እንዲሁም ያለማቋረጥ የሚከናወን

እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህም ተማሪዎች የተሻለ ጤንነት߹ በራስ


መተማመንና የአካል ብቃታችሁ እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ

አለው፡፡

25
የማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት በማለት


መልሱ፡፡

1. ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች መስራት የሰዉነት

ክፍልን ያዳብራል፡፡

2. ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች ከከባድ ወደ ቀላል

ይሰራሉ፡፡

3. መደበኛ የሆነ የምት ድግግሞሽ በተመሳሳይ ቦታና ጊዜ

ይተገበራል፡፡

4. ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች ያለ ሙዚቃ ምት

ማከናወን እንችላለን፡፡
ለ. አጭር መልስ ስጡ
5. በአረንጓዴ አረንጓዴ ጨዋታ ቢጫ ሲባል ምን ይደረጋል?
6. አራቱ ߵመߴ እነማን እንደሆኑ ዘርዝሩ፡፡
34
7. ሦስቱ ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች እነማን ናቸው?

26
3 ምዕራፍ ሦስት

ማህበራዊና ስነ - ልቦናዊ ትምህርት

መግቢያ
ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት ማለት እራስን ማወቅ߹ ስሜትን

መቆጣጠር߹ መልካም ግንኙነትን ለማዳበርና የሌሎችን ሀሳብ

ለመረዳት የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም በሁሉም የማህበረሰብ

ክፍል እውቀትን߹ ክህሎትን߹ በጎ አመለካከትን፣ የሥራ ተነሳሽነትን

የሚያጠነክር የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡


በዚህ ምዕራፍ የሚካተቱ ትምህርት ይዘቶች በጨዋታዎች

በእንቅስቃሴዎች አማካይነት የራስን ግንዛቤ ማዳበር߹ በጨዋታዎችና

በእንቅስቃሴዎች አማካይነት ማህበራዊ ግንዛቤ ማዳበር እና

በጨዋታዎችና በእንቅስቃሴዎች አማካይነት ግንኙነትን ማዳበር


ናቸው፡፡

27
የመማር ውጤቶች ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ
በኋላ፡- ፡
• ስለራሳችሁ አዎንታዊ አመለካከት ታዳብራላችሁ߹
• የሌሎች ፍላጎትና ስሜትን ትረዳላችሁ߹
• የማህበራዊ ግንኙነት ጥቅምን ታስረዳላችሁ፡፡

• የማህበራዊ አመለካከት߹ ባህላዊ ስርዓትንና እሴቶችን


ትረዳላችሁ߹

3.1. በጨዋታዎችና በእንቅስቃሴዎች አማካይነት የራስን


ግንዛቤ ማዳበር

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ


በኋላ፡-
• የራስንና የሌሎችን የባሕርይ ልዩነት ትቀበላላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

ራስን መገንዘብ ማለት ምን ማለት ነው?

የራስን ግንዛቤ ማዳበር ማለት የራስን ባህሪ߹ አስተሳሰብና ስሜትን


በመቆጣጠር የሌሎችን ስብዕና በማክበር በንቃትና ውጤታማ
በሆነ መንገድ የምንተገብረው ነው፡፡ ይህን ለማዳበር የሰዉነት
እንቅስቃሴን በተመጠነና በመደበኛነት ልታከናውኑ ይገባል፡፡

28
ተግባር 1፡- ቤት አልባው /Home-less/
የአሰራር ቅደም ተከተል
ቤትን እንዲወክል የተዘጋጀ አራት ማዕዘን /ክብ/ ቦታ እና
ለማባረሪያ የሚያገለግል መጫወቻ ስፍራ ይኖራል፡፡
• ተማሪዎችን ለሁለት በመከፈል አንደኛው ቡድን ቤት ያለው
ሌላኛው ቤት አልባ ይሆናል߹
• ቤት አልባው ቡድን ውስጥ ያላችሁ ተማሪዎች አባራሪ፤ ቤት
ያላቸው ደግሞ ተባራሪ ትሆናላችሁ߹
• ቤት ያላችሁ ተማሪዎች ከቤታችሁ ስትወጡ ቤት አልባዎች
እናንተን በማባረር ሲነኩዋችሁ ቤት ያላቸው ይሆናሉ߹
• በዚህ ሁኔታ እየተተካችሁ ጨዋታው ይቀጥላል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

-
ተግባር 2፡ ሮጦ ማምለጥ
የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች በሦስት ቡድን ትከፈላላችሁ፡፡ ከዚያም ሁለቱ ቡድን
በአራት ሜትር ርቀት ፊት ለፊት በረድፍ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ
ትቆማላችሁ፡፡
• በረድፍ ከቆማችሁት ሁለት ቡድኖች አንደኛው ቡድን
ትናንሽና ቀለል ያሉ ኳሶችን ይይዛሉ፣
• ከሦስተኛው ቡድን በየተራ አንድ አንድ ተማሪ በሁለቱ
ቡድኖች መካከል በኳስ ሳይመቱ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋሉ፣
• በረድፍ የቆማችሁ ተማሪዎች የሚወረወር ኳስን በመያዝ
በመሀል የሚያልፉት ላይ ትወረውራላችሁ፣
29
• በዚህ ሂደት በኳስ የተመቱ ተማሪዎች ከጨዋታ እየወጡ
መጨረሻ ላይ የቀረ ተማሪ አሸናፊ ይሆናል፣
• ከዚያም እየተቀያየራችሁ ሁሉም ቡድን በተራ ይደርሳችኃል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 16 ፡- ሮጦ ማምለጥ

ተግባር 3፡- ጌሾ - ጌዶ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች ለሁለት ተከፍላችሁ አንዱ ቡድን ጌሾ ሌላኛው ጌዶ የሚል
ስያሜ ትይዛላችሁ፡፡ በሦስት ሜትር ርቀት በረድፍ ፊት
ለፊት ትቆማላችሁ፤ ከሁለቱም ቡድን ጀርባ 10 ሜትር ርቀት ላይ
ቤት ይኖራችኃል፣
• ጨዋታውን ለመጀመር የመጀመሪያውን ፊደል ߵጌߴ ከአራት
ጊዜ ያላነሰ መጥራትና አዘናግቶ የመጨረሻውን ፊደል
መጥራት፣
• ስሙ የተጠራ ቡድን ተባራሪ ያልተጠራ አባራሪ ይሆናል፣
30
• ቤታችሁ ሳትደርሱ የተነካችሁ ተማሪዎች ከጨዋታ ውጭ
ትሆናላችሁ፣
• በተራም ስሞቹን በማቀያየር ሁለቱም ቡድን ትጫወታላችሁ߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 17፡- የጌሾ-ጌዶ ጨዋታ

የግምገማ ጥያቄዎች

1. የራስን ግንዛቤ ለማዳበር ምን ማድረግ አለብን?

2. የራስን ግንዛቤ ማዳበር ምን ማለት ነው?

3.2. በጨዋታዎችና በእንቅስቃሴዎች አማካይነት ማህበራዊ


ግንዛቤን ማዳበር

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ


በኋላ፡-
• የሌሎችን ሀሳብ߹ ባህልና ልዩነትን ትቀበላላችሁ߹

31
የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ
ማህበራዊ ግንዛቤ ምን ጠቀሜታ አለው?

ማህበራዊ ግንዛቤ ማለት ከጎረቤቶቻችን߹ ከአካባቢ ሰዎች

እንዲሁም ከክፍል ጓደኞቻችን እና ከሌሎችም ጋር መልካም

ቅርርብ የመፍጠር ጠቀሜታን የምንረዳበት ነው፡፡ አካላዊ

እንቅስቃሴ በሰዎች መካከል አዎንታዊ ግንኙነትን ያጎለብታል፡፡

ይህን መልካም ግንኙነት ለመፍጠር በጋራ (በቡድን) የሚከናውኑ

አካላዊ እንቅስቃሴዎች የበለጠ ጠቃሚ ናቸው፡፡

ተግባር 1፡- ዓሳና ዓሳ አጥማጅ /fish and fisher/

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎችን ሁለት ቡድን ትመሰርታላችሁ߹

• አንደኛው ቡድን ዓሳ አጥማጅ /አባራሪ/ ሌላኛው ቡድን ዓሳ


ተባራሪ/ ትሆናላችሁ፣
• አባራሪው ቡድን እጅ ለእጅ በመያያዝ በማጥበብ እና
በማስፋት ተባራሪዎችን መማረክ /ዓሳዎችን ማጥመድ/፣
• የተማረካችሁ ተማሪዎች ከጨዋታው ትወጣላችሁ፣
• መጨረሻ የቀረ ተማሪ አሸናፊ ይሆናል፣
• ከዚያም ተባራሪው አባራሪ በመሆን ጨዋታው ይቀጥላል፣
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

32
ስዕል 19፡- ዓሳና ዓሳ አጥማጅ ጨዋታ

ተግባር 2፡- ቤተሰብ መመስረት


የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች ርቀታችሁን ጠብቃችሁ በአንድ አከባቢ ቀለል ያለ

ሶምሶማ ታደርጋላችሁ፣

• መምህሩ/ሯ እያዘበራረቀ ከተማሪዎች ቁጥር አሳንሶ/ሳ

ሲጠራ/ስትጠራ በተጠራው ቁጥር ልክ ተማሪዎች

ከጓደኞቻችሁ ጋር ትያያዛላችሁ፣
• ከተጠራው ቁጥር ዉጭ የሆነ/ች ተማሪ ከጨዋታው

ትወጣላችሁ፣
• መጨረሻ ላይ የቀረው/ችው አሸናፊ ይሆናል/ትሆናለች፡፡ በዚህ
መሰረት ጨዋታው ይቀጥላል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

33
ስዕል 20፡- ቤተሰብ መመስረት ጨዋታ

ተግባር 3፡- አባ ያዕቆብ

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች ክብ በመስራት ትቆማላችሁ፣

• አንድ ተማሪ መሀከል እንዲቆም/ድትቆም/ ማድረግ፣

• በክቡ መሀከል የቆመው/ችው/ ተማሪ ያዕቆብ በማለት

ትዕዛዝ መስጠት፣ ለምሳሌ፡- ያዕቆብ ጸጉርህን አበጥር/ሪ

ፊትህን ታጠብ/ቢ

አንድ እጅህን አንሳ/ሺ

እግርህን ዘርጋ/ጊ
ተቀመጥ/ጭ…ወዘተ
34
• በክቡ መኃል የቆመው/ችው የሚያዘውን/ምታዘውን ያለ

ስህተት መስራት፣

• ያዕቆብ የሚለው ስም ሳይጠራ አድርጉ ቢባል ትዕዛዙ

በተግባር አይውልም፣

• ትዕዛዙን ያልተከተለ ከጨዋታ ውጭ ይሆናል፣

• እስከ መጨረሻ የቆየ የጨዋታው አሸናፊ በመሆን መካከል

በመቆም ያጫውታል/ታጫውታለች߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት


መጨረስ፡፡

ስዕል 21፡- አባ ያዕቆብ

የግምገማ ጥያቄዎች

1.ማህበራዊ ግንዛቤ ምንድን ነው?

2.ማህበራዊ ግንዛቤ በምን ዓይነት እንቅስቃሴ ይዳብራል?

35
3.3. በጨዋታዎችና በእንቅስቃሴዎች አማካይነት ግንኙነትን
ማዳበር

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ


በኋላ:-
• ከሌሎች ጋር አዎንታዊ በሆነ መልኩ ትተባበራላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ


እንቅስቃሴዎችን በምን ዓይነት ሁኔታ ልንሰራ እንችላለን?

አካላዊ እንቅስቃሴን በግልም ሆነ በቡድን ማከናወን ይቻላል፡፡

በተለይ በቡድን የሚሰራ አካላዊ እንቅስቃሴ ከሰዎች ጋር ያለንን

ግንኙነት በማዳበር የሰዎችን ስሜት የመረዳት አቅምን

ያጎለብታል፡፡ በዚህም የተነሳ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመወሰን

አቅማችን ኃላፊነት የተሞላበት እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ

አለው፡፡
ተግባር 1፡- ኳስ በእጅ ወደ ኋላ ማቀበል
የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በረድፍ በመሆን መቀመጥ፣

• ከፊት ያለው/ችው ተማሪ በጭንቅላቱ/ቷ ላይ ከኋላ

ላለው/ችው ተማሪ ኳስ ማቀበል፣

• የተቀበለውም/ችው ለቀጣይ በማቀበል በዚህ ሁኔታ እስከ

መጨረሻው መቀጠል፣

36
• የመጨረሻ ተማሪ ኳሱን ይዞ/ዛ ከፊት በመምጣትና

በመቀመጥ ወደ ኋላ ያቀብላል/ ታቀብላለች፣

• በዚህ ሁኔታ በመቀባበል ጨዋታው ይቀጥላል߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 22፡- ኳስን በእጅ ወደኋላ ማቀበል

ተግባር 2፡- ኳስ መልቀም

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች ፊት ለፊት በሁለት ረድፍ ትቆማላችሁ፣


• በአንዱ ጠርዝ በኩል ለሁለቱም ረድፍ እኩል ቁጥር ያላቸው
ኳሶች ይቀመጣሉ፣
• ከዚያም ኳሱ ባለበት በኩል ያላችሁ የመጀመሪያ ተማሪዎች
ኳሱን በማንሳት አጠገባችሁ ላለ ጓደኛ ታቀብላላችሁ፣

37
• የተቀበሉ ተማሪዎች አንዱ ለአንዱ በመስጠት እስከ

መጨረሻው ተማሪ ድረስ ትቀባበላላችሁ፣

• የመጨረሻ ተማሪዎች ጋር ኳሱ ሲደርስ የተዘጋጀው ቦታ ላይ

ታስቀምጣላችሁ፣
• በዚህ ጊዜ የመጀመሪያ ተማሪዎች ሌላ ኳስ በማንሳት እንደ

መጀመሪያው ታቀብላላችሁ፣

• በዚህ ሁኔታ ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 23፡- ኳስ የመልቀም ጨዋታ

ተግባር 3፡- ከአደጋ መጠንቀቅ


የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች ርቀታችሁን ጠብቃችሁ በተዘጋጀው ክብ ዙሪያ
መቆምና አደገኛ የተባለውን ቦታ በምልክት መለየት፣

38
• ተማሪዎች በክቡ ዙሪያ በሶምሶማ እንቅስቃሴ
ታደርጋላችሁ፣

• ቁም የሚል ምልክት ወይም ድምፅ ሲሰጥ መቆም፣


• በተሰጠው የቁም ትዕዛዝ ወይም ምልክት ስትቆሙ
አደገኛ ቦታ የቆመ ከጨዋታ ውጭ ማድረግ፣
• በዚህ አኳኋን መጨረሻ የቀረ አሸናፊ ይሆናል߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት
መጨረስ፡፡

ስዕል 24፡- በክብ ዙሪያ ቆመው የሚያሳይ

የግምገማ ጥያቄዎች

1. በቡድን የሚሰራ እንቅስቃሴ ምን እንድናዳብር ይረዳናል?

2. አካላዊ እንቅስቃሴ እንዴት ማከናወን እንችላለን?

39
የምዕራፉ ማጠቃለያ

ማህበራዊና ስነልቦናዊ ትምህርት ተማሪዎች በእውቀት߹ በክህሎት߹

በጎ አመለካከት እንዲሁም መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው

ያስችላል፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ የራስን ባሕርይና አስተሳሰብ

ለማዳበር እንዲሁም ስሜት ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ

አለው፡፡ የቡድን እንቅስቃሴ በግል ከሚሰራ በበለጠ አዎንታዊ

ግንኙነት የመፍጠር አቅም አለው፡፡ በተጨማሪ አካላዊ እንቅስቃሴ

የሰዎችን ስሜት የመረዳትና የመወሰን ብቃትን ያጎለብታል፡፡

40
የማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች እዉነት ወይም ሐሰት በማለት


መልሱ፡፡
1. የሰዉነት እንቅስቃሴ አካልን ብቻ ሳይሆን አዕምሮንም
ያዳብራል፡፡
2. ጨዋታዎችና እንቅስቃሴዎች መልካም ግንኙነት ያጠናክራሉ፡፡

3. ስሜትን አለመቆጣጠር የሚያስከትለው ችግር የለም፡፡

4. የአካል እንቅስቃሴ በግል ብቻ የምናከናውነው ተግባር ነው፡፡

5. በቡድን የሚሰራ እንቅስቃሴ የሌላውን ስሜት እንድንገነዘብ


ይረዳል፡፡
ለ. ትክክለኛውን መልስ ምረጡ
6. በዓሳ አጥማጆች ጨዋታ አሸናፊ ማነው?
ሀ. ያልተማረከ ለ. የተማረከ ሐ. መልሱ
የለም
7. ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያዳብር ጨዋታ ምረጡ?

ሀ.ዓሳ አጥማጆች ለ.ቤተሰብ መመስረት ሐ.


ሁሉም
8. በቤት አልባው ጨዋታ ጊዜ አራት ማዕዘን ውስጥ የሚገቡ

ተማሪዎች
ሀ. አባራሪዎች ለ.ተባራሪዎች ሐ.ሁለቱም

41
4 ምዕራፍ አራት

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ


መግቢያ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአጠቃላይ ጤንነትን ߹ በመጠበቅ

የዕለት ተዕለት ተግባርን በብቃት እንድንወጣ የሚያስችል አካላዊ

እንቅስቃሴ ነው፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ጤናን ከመጠበቅ አንፃር

ዘመናዊ ከሚባሉት የጤና አጠባበቅ ዘዴዎች የቀደመና የተሻለ

ነው፡፡ የአካል ብቃት የልብና ሳንባ߹ የጡንቻ ብርታት߹ የጡንቻ

ጥንካሬ߹ የመተጣጠፍና መዘርጋት߹ በሽታን የመከላከል አቅም߹

ድካምና ጭንቀት የመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በዚህ

ተጠቃሚ ለመሆን በመደበኛነት አካላዊ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ

ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
በዚህ ምዕራፍ የሚካተቱ የትምህርት ይዘቶች ለልብና የደም ሥር

ብርታት የሚሰራ እንቅስቃሴ߹ የጡንቻ ብርታት߹ መጣጠፍና

መዘርጋት እና ቅልጥፍና ናቸው፡፡

42
የመማር ውጤቶች፡ ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በጥንቃቄ ትለማመዳላችሁ፣

• በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመሳተፍ መበርታታትን ታሳያላችሁ፣

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትን ትወዳላችሁ፣

4.1 ለልብና የአተነፋፈስ ብርታት የሚሰራ እንቅስቃሴ


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ርዕስ ትምህርት ከተማራችሁ

በኋላ፡-
• ለልብና የአተነፋፈስ ብርታት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን
ትዘረዝራላችሁ ፣
• በገመድ ዝላይና ጉልበትን በማንሳት እንቅስቃሴ የልብን እና
የአተነፋፈስ ብርታትን ታሻሽላላችሁ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ


የልብና የአተነፋፈስ ብርታት እንቅስቃሴ ምን ጥቅም አለው?
የልብና የደም ሥር ብርታት የሚያዳብር እንቅስቃሴ ጫናው ቀላል

የሆነና ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ የልብና

የሳንባ ብርታትን ማሻሻል ይቻላል፡፡ የልብና የደም ሥር ብርታት

ሲሻሻል የዕለት ተዕለት ተግባራችንን በአግባቡ መወጣት

እንችላለን፡፡ እንዲሁም ከልብና የደም ቧንቧ ጋር ተያያዥነት

ባላቸው በሽዎች እንዳንጠቃ ይረዳናል፡፡

43
ተግባር 1፡- የገመድ ዝላይ

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በሁለት ተርታ ትሰለፋላችሁ፣

• ከሁለቱም ተርታ አንድ አንድ ተማሪዎች ርቀታችሁን

ጠብቃችሁ ወደ ፊት ትወጣላችሁ߹

• ሁለቱ ተማሪዎች አንድ አንድ ገመድ በመያዝ ራሳችሁን

ችላችሁ ትዘላላችሁ߹

• የዘለላችሁ ተማሪዎች ወደ ኋላ በመመለስ ሁላችሁም ተሳትፎ

ታደርጋላችሁ߹
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 25፡- የገመድ ዝላይ

44
ተግባር 2፡- የኳስ ለቀማ ጨዋታ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች ፊት ለፊት በአራት አቅጣጫ ትቆማላችሁ፣
• ከቆማችሁበት ጀርባ ለኳስ ማጠራቀሚያ የሚሆን ቅርጫት
ይቀመጣል߹
• በቆማችሁት ተማሪዎች መሀል አማካይ ቦታ ላይ በርከት ያሉ
ትናንሽ ኳሶች ይቀመጣሉ߹
• ከዚያም እኩል በመጀመር ሁለት ሁለት ኳሶች ከመሀል ወደ
ማጠራቀሚያ ቅርጫት ትሰበስባላችሁ߹
• በመጨረሻም ብዙ የለቀመ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት


መጨረስ፡፡

ስዕል 26፡- የኳስ ለቀማ ጨዋታ

45
ተግባር 3፡- ጉልበትን አጥፎ መነሳት
የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በረድፍ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሰለፍ፣

• እግራችሁን በትከሻ ስፋት በመክፈት እጃችሁን ወደ ፊት

ዘርግታችሁ መቆም፣

• አንድ ሲባል ከወገባችሁ ቀጥ በማለት ጉልበታችሁን አጠፍ

ማድረግ፣

• ሁለት ሲባል ቀጥ ብላችሁ መቆም፣

• በዚህ ሂደት እንቅስቃሴውን መቀጠል߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 27፡- ጉልበትን አጥፎ መነሳት

46
ተግባር 4፡- የካንጋሮ ዝላይ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በ4 ተርታ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሰለፍና ከፊት
ለፊታችሁ በሦስት ሜትር ርቀት ላይ ከ4-6 የሚደርሱ ትናንሽ
ኳሶች ማስቀመጥ፣
• ከፊት ያላችሁ በጆንያ ውስጥ መቆም፣

• በፊሽካ ድምፅ በመጀመር በጆንያ ውስጥ እየዘለላችሁ ኳሶች

ያሉበት ቦታ መድረስ፣
• ከዚያ የተቀመጡ ኳሶችን ጆንያ ውሰጥ መሰብሰብና ቀድሞ

ወደ ተነሳችሁበት ቦታ መመለስ፣
• ፈጥኖ/ና ለጨረሰ/ች ተማሪ ማጨብጨብ፣

• ሁላችሁም በተራ መስራት߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት


መጨረስ፡፡

ስዕል 28፡- የካንጋሮ ዝላይ


47
የግምገማ ጥያቄዎች

1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ምን ጥቅም አለው?

2. የልብና የአተነፋፈስ ብርታት እንዴት ሊዳብር ይችላል?

4.2.የጡንቻ ብርታት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህን ርዕስ ከተማራችሁ


በኋላ፡-
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት አዎንታዊ ስሜትን
ታዳብራላችሁ፣
• የጡንቻንና የአጥንትን ጥንካሬ ታሻሽላላችሁ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ


የጡንቻ ብርታት ማለት ምን ማለት ነው?

የጡንቻ ብርታት ማለት ጫናን ተቋቁሞ ረዘም ላለ ጊዜ ያለ

ድካም እንቅስቃሴን የማከናወን አቅም ነው፡፡ የጡንቻ ብርታት

የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በአግባቡ እንድናከናውን ያስችለናል፡፡

ለምሳሌ፡- መራመድ߹ መሮጥ߹ መሸከም߹ መቆፈር߹ መጫወት߹


…ወዘተ ናቸው፡፡ ይህን የጡንቻ ብርታት ለማዳበር የተለያዩ

እንቅስቃሴዎችን ከመደበኛው ጊዜ በበለጠ መስራት ጠቃሚ ነው፡፡

ተግባር 1፡- በእጅ የመቀስ ቅርፅ መስራት


የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች በረድፍ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ ትቆማላችሁ፣

48
• አንድ ሲባል ሁለት እጅን በትከሻ ከፍታ በማድረግ ወደ ፊት
መዘርጋት፣
• ሁለት ሲባል ሁለት እጅን በትከሻ ከፍታ ወደ ጎን መዘርጋት፣

• ሦስት ሲባል ሁለት እጅን ከጭንቅላት ላይ በማሳለፍ የመቀስ


ቅርፅ መስራት፣
• ይህን በድግግሞሽ ትሰራላችሁ፣
• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 29፡- በእጅ የመቀስ ቅርፅ የመስራት ጨዋታ

ተግባር 2፡- በደረት ተኝቶ ከደረት በላይ ቀና ማለት

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች በረድፍ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መሬት ላይ በደረት

ትተኛላችሁ፣

49
• አንድ ሲባል በሁለት እጅ በመደገፍ ከተኛችሁበት ቀና ማለት፣
• ሁለት ሲባል በደረት መተኛት፣
• በድጋሚ አንድ ሲባል በሁለት እጅ በመደገፍ ከተኛችሁበት
ቀና ትላላችሁ፣
• በዚህ ሁኔታ በድግግሞሽ ትሰራላችሁ߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ


63
እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

ስዕል 30፡- በደረት ተኝቶ በእጅ በመደገፍ ቀና ማለት

የግምገማ ጥያቄዎች

1.የ ጡንቻ ብርታት ምን እንድናከናውን ያስችለናል?


2.በ ደረት ተኝቶ ከደረት በላይ ቀና ማለት የትኛውን የሰዉነት
ክፍል ያዳብራል?

4.3. የመተጣጠፍና የመዘርጋት እንቅስቃሴ

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህን ርዕስ ከተማራችሁበኋላ፡-

• የመተጣጠፍና መዘርጋት እንቅስቃሴን ታሻሽላላችሁ፣

50
የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ
መታጠፍና መዘርጋት ማለት ምን ማለት ነው? መተጣጠፍና
መዘርጋት ማለት የጡንቻና የመገጣጠሚያ እስከ መጨረሻው የመታጠፍና
መዘርጋት ብቃት ነው፡፡ ይህ የመተጣጠፍና መዘርጋት ክህሎት ሰዉነት ከሞቀ
በኋላ በማሳሳብ እንቅስቃሴ የሚሻሻልና የሚዳብር ነው፡፡ በመሆኑም የዕለት
ሥራችንን በአግባቡ እንድንወጣ ያስችለናል፡፡

ተግባር 1፡- የላይኛው የሰዉነት ክፍልን ማሳሳብ

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች በረድፍ በመሰለፍ እግራችሁን በትከሻ ስፋት መክፈት፣


• ሁለት እጃችሁን ጣት ለጣት በማያያዝ በትከሻ ከፍታ ወደ
ፊት ማሳሳብ፣
• እጃችሁን ጣት ለጣት በማያያዝ ከጭንቅላታችሁ በላይ
ማሳሳብ፣

• ቀኝ እጃችሁን በትከሻ ላይ ወደ ጀርባ በማሳለፍ ግራ እጃችሁ

በጎን በኩል ወደ ጀርባ በመውሰድ ከቀኝ እጅ ጋር በማያያዝ

ማሳሳብ፣

• ግራ እጃችሁን በትከሻ ላይ ወደ ጀርባ በማሳለፍ ቀኝ እጃችሁ

በጎን በኩል ወደ ጀርባ በመውሰድ ከግራ እጅ ጋር በማያያዝ

ማሳሳብ፣

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት

መጨረስ፡፡

51
ስዕል 31፡- የላይኛው የሰዉነት ክፍልን ማሳሳብ

ተግባር 2፡- የወገብ ክፍልን ማሳሳብ


የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች በረድፍ እግራችሁን ዘርግታችሁ ትቀመጣላችሁ፣
• መጀመሪያ ሁለት እጃችሁን በትከሻ ከፍታ ወደ ጎን
መዘርጋት፣
• ከዚያም ከወገባችሁ ወደ ቀኝና ግራ በመዞር ትንሽ ቆይታ
ታደርጋላችሁ፣
• በቀጣይ ሁለት እጃችሁን ወደ ፊት ዘርግታችሁ የእግር
ጣታችሁን ላይ ለመድረስ ጥረት ታደርጋላችሁ፣
• በዚህ ጊዜ ጉልበት መታጠፍ የለበትም߹

• በመጨረሻም ሰዉነትን የማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ በመስራት


መጨረስ፡፡

52
ስዕል 32፡- የወገብ ክፍልን ማሳሳብ

የግምገማ ጥያቄዎች

1. የመተጣጠፍና መዘርጋት ክህሎት እንዴት ማዳበር

ይቻላል?

2. የመተጣጠፍና መዘርጋት ክህሎት ምን ጠቀሜታ


አለው ?
4.4.ቅልጥፍና
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህን ርዕስ ከተማራችሁ
በኋላ፡-
• በፍጥነት የመታጠፍ እንቅስቃሴን ታሻሽላላችሁ ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

53
ቅልጥፍና ማለት ምን ማለት ነው?
ቅልጥፍና በፍጥነት አቅጣጫን በመቀየር የሚከናወን አካላዊ
እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ የአካል ብቃት የሰዉነት ሚዛን መጠበቅ߹
ፍጥነት߹ ጥንካሬ߹ ብርታትንና የአካል ክፍል መቀናጀትን ያካተተ
ክህሎት ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ክህሎት ለማዳበር በመደበኛነት
አካላዊ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ተግባር 1 ፡- መሀረቤን ያያችሁ
የአሰራር ቅደም ተከተል
• ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ መሬት ላይ

ክብ ሰርታችሁ ትቀመጣላችሁ፣
• አንድ ተማሪ ከተቀመጣችሁት መካከል በመምረጥ መሃረብ

ወይም ጨርቅ ማስያዝ߹

• መሀረቤን ያያችሁ እያለ/ች የተቀመጣችሁትን ተማሪዎች

በእርምጃ ይዞራል/ትዞራለች߹
• የተቀመጣችሁት ተማሪዎች አላየንም እባካችሁ በማለት ምላሽ
ትሰጣላችሁ߹
• ክቡን የሚዞረው/ምትዞረው የያዘውን/የያዘችውን ጨርቅ
ከተቀመጣችሁት ተማሪዎች አንደኛው ጀርባ ጋር አስቀምጦ/ጣ
መሮጥ߹
• መሃረብ የተጣለበት ተማሪ ተነስቶ/ታ መጀመሪያ ከተነሳበት

ሳይደርስ/ሳትደርስ በመሃረብ ለመምታት ማባረር߹


• በዚህ ጊዜ ካልደረሰ/ች መሃረቤን ያያችሁ በማለት መቀጠል߹
• በመጨረሻም ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ መጨረስ፡፡

54
ስዕል 33፡- መሀረቤን ያያችሁ

ተግባር 2 ፡- የሠንሠለት ጨዋታ


የአሰራር ቅደም ተከተል

• ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ በረድፍ

መሰለፍ፣

• ከረድፉ ፊት ለፊት በአራት ሜትር ርቀት ላይ ቅምብቢት

ይቀመጣል߹

• በፊሽካ ድምፅ ከፊት ያላችሁ ተማሪዎች በሩጫ ቅምብቢቱን

በመዞር መመለስና ሌላ ተማሪ በመያዝ በድጋሜ ቅምብቢቱን

መዞር߹
• በዚህ ሁኔታ እርስ በእርስ እየተያያዛችሁ በፍጥነት የጨረሰ ረድፍ

አሸናፊ ይሆናል߹

• በመጨረሻም ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ መጨረስ፡፡

55
ተግባር 3 ፡- የጠመዝማዛ ሩጫ

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ በረድፍ

መሰለፍ፣

• ከፊት ያላችሁ ተማሪዎች ከተቀመጣችሁበት በመነሳት ከኃላችሁ

የተቀመጡትን ተማሪዎች በመካከላቸው በጠመዝማዛ

በመሮጥና በድጋሜ በመመለስ ቦታችሁ ላይ ትቀመጣላችሁ߹

• በዚህ ሁኔታ ሁላችሁም ተማሪዎች በጠመዝማዛ በመሮጥና

ቦታችሁ በመመለስ ቀድሞ የጨረሰ ረድፍ አሸናፊ ይሆናል߹

• በመጨረሻም ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ መጨረስ፡፡

ተግባር 4 ፡- ߵአያ ጅቦߴ ጨዋታ

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ ክብ

መስራትና መቆም߹

56
• አንድ ተማሪ መምረጥና ክቡ መሃል ላይ እንደ አያ ጅቦ

የሚጫወት ማስቀመጥ߹

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- እንሂድ (2) ወደ ጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ

አያ ጅቦ አለህ?

• አያ ጅቦ፡- አዎ

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- ምን ትሰራለህ?

• አያ ጅቦ፡- ከእንቅልፌ እየተነሳሁ

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- እንሂድ (2) ወደ ጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ

አያ ጅቦ አለህ?

• አያ ጅቦ፡- አዎ

• ዙሪያውን የቆሙት፡- ምን ትሰራለህ?

• አያ ጅቦ፡- አልጋዬን እያነጠፍኩ


• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- እንሂድ (2) ወደ ጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ

አያ ጅቦ አለህ?
• አያ ጅቦ፡- አዎ

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- ምን ትሰራለህ?

57
• አያ ጅቦ፡- ፊቴን እየታጠብኩ

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- እንሂድ (2) ወደ ጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ

አያ ጅቦ አለህ?

• አያ ጅቦ፡- አዎ

• ዙሪያውን የቆማችሁት፡- ምን ትሰራለህ?

• አያ ጅቦ፡- እናንተን ልበላ

• በዚህ ጊዜ ዙሪያውን የቆማችሁት በአያ ጅቦ ላለመያዝ

ትሮጣላችሁ የተያዘ ተማሪ እንደ አያ ጅቦ በመሆን ጨዋታው

ይቀጥላል߹

• በመጨረሻም ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ መጨረስ፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች

1. ቅልጥፍና ምን ምን የሚያካትት ክህሎት ነው?

2. ቅልጥፍናን ለማዳበር ምን ማድረግ አለብን?

58
የምዕራፉ ማጠቃለያ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአጠቃላይ ለሰው ልጅ ጤንነት፣ የአካል

ብቃት መሻሻል እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጎለብት

ነው፡፡ በመደበኛነት አካላዊ እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ጤናማ

መሆንን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የልብና

የደም ሥር ብርታት፣ የጡንቻ ብርታት፣ መታጠፍና መዘርጋትን

እንዲሁም ቅልጥፍናን የሚያሻሽል በመሆኑ ይህንን ሊያዳብሩ

የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ አድርጋችኃል፡፡

59
የማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት በማለት


መልሱ፡፡
1.የአካል ብቃት የዕለት ተግባርን በአግባቡ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡
2.አካላዊ እንቅስቃሴ ከዘመናዊ ጤና አጠባበቅ የቀደመ ነው፡፡
3.የአካል ብቃት ጤንነት እንድንጠብቅ ብቻ ይረዳናል፡፡

ለ. ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡


4.የአካል ብቃት ጥቅም ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ጤንነት ለ.መወፈር ሐ. መልሱ የለም


5.የአካል ብቃት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. የጡንቻ ብርታት ለ. የልብ ብርታት ሐ. ሁሉም


6.የልብና የደም ሥር የሚያዳብር እንቅስቃሴ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ገመድ መዝለል ለ. ኳስ ለቀማ ሐ. ሁሉም


7.የጡንቻ ብርታት ምን እንድናከናውን ያስችለናል?
ሀ. መተኛት ለ. መሸከም ሐ. መልስ የለም
8.የመታጠፍና መዘርጋት ክህሎትን የሚያዳብር እንቅስቃሴ መቼ

መስራት አለብን?
ሀ. ሰዉነታችን ከሞቀ በኋላ ለ. ከእንቅልፋችን እንደተነሳን

ሐ. ሁሉም

60
5 ምዕራፍ አምስት

ጅምናስቲክ
መግቢያ
የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ በመገለባበጥና በመተጣጠፍ የሚከናወን

ሲሆን አጥንት߹ ጡንቻ እና ጅማቶቻችን በአግባቡ ሥራቸውን

እንዲሰሩ እንዲሁም ጥንካሬና ብርታት እንዲኖራቸው ይረዳናል፡፡

ጅምናስቲክ የተሟላ ጤንነት፣ ጥንካሬ፣ የተስተካከለ ቅርፅና ቁመና

እንዲኖር የሚያደርግ የእንቅስቃሴ ክህሎት ነው፡፡ የጅምናስቲክ

እንቅስቃሴን ከመስራት በፊት የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ

ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ፡- የተሟላ የስፖርት ትጥቅ መልበስ፣ ሰዉነት

ማሟሟቅ፣ የሚሰራውን የእንቅስቃሴ ዓይነት ለይቶ ማወቅ፣

እራስን ለእንቅስቃሴ ማዘጋጀት እና ከቀላል ወደ ከባድ መስራት

ወዘተ… ናቸው፡፡

በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ የትምህርት ይዘቶች መሠረታዊ

የጅምናስቲክ ክህሎት በቀላል ድግግሞሽ እና የተወሰነ የእንቅስቃሴ

ሥራና አስፈላጊነት ናቸው፡፡


61
የመማር ዉጤቶች፡ ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• መሠረታዊ የጅምናስቲክ ክህሎትን ትሰራላችሁ፣


• ወደፊት የመግፋትና ሚዛን የመጠበቅ እንቅስቃሴን ትሰራላችሁ፣

• የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ጥቅምን ትረዳላችሁ፣

5.1 መሠረታዊ የጅምናስቲክ ክህሎት በቀላል ድግግሞሽ


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ:-
• መሠረታዊ ሚዛን የመጠበቅ፣ የመንከባለል፣ የመዞር፣

የመለጠጥ፣ አቀበት የመውጣት እና ክብደት ያላቸው

ዕቃዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ተግባራዊ


እንቅስቃሴን ታሻሽላላችሁ፣
• ራሳችሁን በመቆጣጠር ወደ ፊት ትንከባለላላችሁ፣

• ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወደ ኋላ የመንከባለል እንስቃሴን

ትሰራላችሁ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

መሠረታዊ ጅምናስቲክ ምን ማለት ነው?

መሠረታዊ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች ሰፊ ቦታ እና ከፍተኛ

ወጪ የማይጠይቁ በማንኛውም ቦታና የዕድሜ ደረጃ በወንዶች


እና በሴቶች እንዲሁም በህፃናት የሚሰሩ እንቃስቃሴዎች ናቸው፡፡

መሰረታዊ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ በቀጣይ ለምናከናውነው ከባድ

62
የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ መሠረት የምንጥልበት ነው፡፡ በመሆኑም
ችሎታና ዕድሜ በሚመጥን መልኩ አስፈላጊውን ጥንቃቄና ድጋፍ

በማድረግ በየዕለቱ ከምታከናውኗቸው እንቅስቃሴዎች ጋር

በማዛመድ በቀላሉ መተግበር ይቻላል፡፡

ተግባር 1 ፡- በፍራሽ ላይ አቋርጦ መራመድ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ ተራ በተራ ፍራሽ

ላይ ትቆማላችሁ፣
• ሚዛን ለመጠበቅ እግራችሁን በትከሻ ስፋት ልክ መክፈት፣
• ቀኝ እግር ወደፊት ሲራመድ ግራ እጅ ወደ ፊት በመዘርጋት
እንዲቀናጅ ማድረግ፣
• በተመሳሳይ መልኩ ግራ እግርን ከቀኝ እጅ ጋር እንዲቀናጅ
ማድረግ፣
• በዝግታ በመራመድ ፍራሹን ማቋረጥ፣
• በድግግሞሽ መስራት እና በመጨረሻ ሰዉነታችሁን
አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ስዕል 35፡-በፍራሽ ላይ አቋርጦ መራመድ

63
ተግባር 2፡- በፍራሽ ላይ መሮጥ

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ ርቀታችሁን

ጠብቃችሁ መሰለፍ߹

• ፍራሽ ላይ የሰውነታችሁን ሚዛን ጠበቃችሁ መራመድ߹

• ከዚያም ፍራሹ ላይ በዝግታ መሮጥ፣

• እንቅስቃሴውን በመደጋገም መስራት፣

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ስዕል 36፡- በፍራሽ ላይ መሮጥ

64
ተግባር 3፡- በፍራሽ ላይ መንከባለል

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ ከፍራሹ ፊት

ለፊት ትሰለፋላችሁ፣

• ከፊት ያላችሁ ተማሪዎች በሆድ ፍራሽ ላይ መተኛት߹

• ሁለት እጅን ከራስ በላይ ቀጥ አድርጋችሁ መዘርጋት߹

• ከዚያም ፍራሹ ላይ መንከባለል߹

• በተመሳሳይ ሁላችሁም መስራት߹

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ስዕል 37፡- በፍራሽ ላይ መንከባለል

65
ተግባር 4፡- ከከፍታ ላይ በሁለት እግር ዘሎ ማረፍ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች የሰዉነት ማሟሟቂያ ከሰራችሁ በኋላ ርቀታችሁን

ጠብቃችሁ በተርታ መሰለፍ፣


• ሰዉነት ወደ ላይ በመሳብ ተረከዝ ወደ ላይ እና ወደ ታች

ማድረግ፣
• ጉልበትን በመጠኑ በማጠፍ ባላችሁበት ወደ ላይ መዝለልን

በተደጋጋሚ መስራት፣

• እጅን ከኃላ ወደ ፊት በመወርወር በሁለት እግር ከፍራሹ

ላይ መዝለል፣

• እንቅስቃሴውን ሁላችሁም በተደጋጋሚ መስራት፣

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ስዕል 38፡-ከከፍታ ላይ በሁለት እግር ዘሎ ማረፍ

66
ተግባር 5፡- በተዳፋትና በተስተካከለ ፍራሽ ላይ መገልበጥ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች የሰዉነት ማሟሟቅ ከሰራችሁ በኋላ በረድፍ

ርቀታችሁን ጠብቃችሁ መቆም፣

• እግርን በትከሻ ስፋት ልክ ከፈት ማድረግ፣

• እጅን ወደፊት በማድረግ እና ከክርን አጠፍ ማድረግ፣

• ጉልበትን በማጠፍ በቀኝ ጎን ቀስ በቀስ መሬትን በማስነካት

መገልበጥ እንዲሁም ባልሰራው ግራ ጎን መስራት߹

• በተመሳሳይ መልኩ ተዳፋት ላይ በተቀመጠ ፍራሽ መገልበጥ፣

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ተግባር 6፡- በሦስት ነጥብ ድጋፍ የእንቁራሪት ዝላይ

የአሰራር ቅደም ተከተል

ተማሪዎች የሰዉነት ማሟሟቂያ ከሰራችሁ በኋላ በረድፍ መሰለፍ፣


• ሁለት እግራችሁን በመጠኑ ከፈት ማድረግ፣

• ከጉልበታችሁ ሸብረክ ብላችሁ እጆቻችሁን ወደ ፊት ትይዩ

በማድረግ መሬት ላይ ማስቀመጥ፣

67
• እግራችሁ ወደ ፊት ሲመጣ እጅን ከመሬት በመልቀቅ ወደ

ፊት እንደ እንቁራሪት መዝለል፣

• በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴውን መደጋገም፣

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ፡፡

ስዕል 40፡- የእንቁራሪት ዝላይ

ግምገማ ጥያቄዎች

1. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴን ማን ሊያከናውን ይችላል?


2. ጅምናስቲክ እንዴት ሊሰራ ይችላል?

5.2. የተወሰነ የእንቅስቃሴ ሥራና አስፈላጊነት

68
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• ከፍ ካለ ቦታ ወደኋላ የመንከባለል እንቅስቃሴዎችን


ትለማመዳላችሁ

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

የተወሰነ የእንቅስቃሴ ሥራ ምን ጥቅም አለው?

የተወሰነ የእንቅስቃሴ ሥራ ማለት የተመረጡ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ

ዓይነት ናቸው፡፡ እነዚህም በተለያየ አቅጣጫ߹ ደረጃ߹ ቅርፅና ፍጥነት

የምንሰራቸው ሲሆን የአካል ብቃት ላይ እንድንደርስና የየዕለት

ተግባራችንን በቀላሉ እንድናከናውን የሚረዱን ናቸው፡፡

ተግባር 1፡- የአግዳሚ ዘንግ አያያዝና መንጠላጠል

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች የሰዉነት ማሟሟቂያ ከሰራችሁ በኋላ ርቀታችሁን
ጠብቃችሁ በደረታችሁ ቁመት ልክ በተዘጋጀ አግዳሚ ዘንግ ፊት
መሰለፍ፣
• እግራችሁን በትከሻ ስፋት ከፍታችሁ አግዳሚ ዘንግ ላይ በእጅ
መደገፍ߹

• እጃችሁን ከክርን አጠፍ ማደረግና ከደረት ወደ አግዳሚው

በመጠጋት ወደ ፊት መግፋት߹

69
• በእግር ጣት በመቆም በእጃችሁ የአግዳሚው ዘንግ ላይ

መደገፍ߹

• ሙሉ በሙሉ እግራችሁን በመልቀቅ አግዳሚው ላይ መደገፍ߹

• እንቅስቃሴውን በመደጋገም መስራት፣

• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ መጨረስ፡፡

ስዕል 41፡- የአግዳሚ ዘንግ አያያዝና መንጠላጠል

ተግባር 2፡- እርምጃ እና ግልቢያ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ተማሪዎች የሰዉነት ማሟሟቂያ ከሰራችሁ በኃላ ርቀታችሁን
ጠብቃችሁ መሰለፍ፣

70
• የተለመደውን የእርምጃ አካሄድ ደጋግማችሁ ስሩ፣
• ቀኝ እግራችሁን በማስቀደም በመራመድ አቋቋም

ትቆማላችሁ፣

• ቀኝ እግራችሁ ወደ ፊት ለመራመድ ሲነሳ በፍጥነት የግራ

እግራችሁ /የኋለኛው/ በቦታው ተተክቶ በትይዩ እንዲቀመጥ


ማድረግ፣

• እንቅስቃሴውን በመደጋገም ፍጥነት እየጨመራችሁ

መለማመድ፣
• በመጨረሻ ሰዉነታችሁን አቀዝቅዛችሁ ማጠናቀቅ

ስዕል 42፡- እርምጃ

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የተወሰነ የእንቅስቃሴ ሥራ ምን ጥቅም አለው?

2. የተወሰነ የእንቅስቃሴ ሥራ በምን አይነት ሁኔታ ልንሰራ

እንችላለን?

71
የምዕራፉ ማጠቃለያ

የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ በመገለባበጥና በመተጣጠፍ የሚከናወን

ሲሆን አጥንት߹ ጡንቻ እና ጅማቶቻችን በአግባቡ ሥራቸውን

እንዲሰሩ እንዲሁም ጥንካሬና ብርታት እንዲኖራቸው ይረዳናል፡፡

በመሆኑም የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች ከመሰራታቸው በፊት

የስፖርት ጉዳቶች እንዳይደርሱ ከትዕዛዝ ውጪ የሚሰሩ

እንቅስቃሴዎችን ማስወገድ፣ የሰውነት ማሟሟቂያ መስራት፣


እንዲሁም መምህራንን ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡

72
የማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት


በማለት መልሱ፡፡
1. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ በመገልበጥና በመታጠፍ የሚሰራ ነው፡፡

2. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ሲሰራ ከከባድ ወደ ቀላል መሆን አለበት፡፡

3. መሠረታዊ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ሰፊ ቦታና ከፍተኛ ወጪ

አይጠይቅም፡፡

4. ጅምናስቲክ ዕድሜን በሚመጥን ልክ መሆን አለበት፡፡

ለ. ትክክለኛውን መልስ ስጥ/ጪ

5. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ምን ጥቅም ይሰጣል?

ሀ. ጤንነት ለ. ጥንካሬ ሐ. ሁሉም

6. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ፍራሽ ላይ መንከባለል ለ. መሀረቤን ያያችሁ ሐ. ፍራሽ ላይ መገልበጥ


89

7. ጅምናስቲክ ማን ሊሰራው ይችላል?


90
ሀ. ወንዶች ለ.ሴቶች ሐ. ሁሉም

73
6 ምዕራፍ ስድስት

ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ከተማ


መግቢያ
ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች የማህበረሰብ ክፍሎች
መገለጫ እሴቶች ናቸው፡፡ ይህ እሴት የሠዉ ልጅ የዕለት ተዕለት
ተግባሩን ሲያከናውን የቆየበትና ከህብረተሰቡ እድገት ጋር እያደገና
እየዳበረ የመጣ ነው፡፡

ባህላዊ እንቅስቃሴ እንደ ማህበረሰቡ ልማድ፣ ሃይማኖትና

ወግ በየአካባቢው የተለያየ ነው፡፡ ይህንንም እንቅስቃሴ በሽለላ፣

በማንጎራጎርና በዘፈን በደስታና በሀዘን ጊዜ እንዲሁም በጋራ ስራን

ሲያከናውኑ የሚተገበር እንቅስቃሴ ነው፡፡

ባህላዊ ጨዋታ በሰፈር፣ በአካባቢና በከተማ ደረጃ ወይም ቡድን

በመመስረት የሚከናወን ሲሆን አዕምሮን፣ መንፈስንና አካልን


የሚያበረታ ነው፡፡

በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ የትምህርት ይዘቶች በአዲስ አበባ ከተማ


የሚገኙ የታወቁ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ
ባህላዊ ጨዋታዎች ማድነቅ ናቸው፡፡

74
የመማር ውጤቶች፡ ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች


ጥቅም ታውቃላችሁ߹
• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች
ጥቅም ትወዳላችሁ߹
• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች
ጥቅም ታሳያላችሁ߹

6.1. በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የታወቁ ባህላዊ


እንቅስቃሴዎች
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• በአዲስ አበባ ከተማ የታወቁትን ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና


ጨዋታዎችን ትለያላችሁ߹
• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና
ጨዋታዎችን ታደንቃላችሁ߹

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና እንደ መሆኗ መጠን የተለያዩ

ማህበረሰቦች ይኖሩባታል፡፡ በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ

የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በተለያየ መልኩ መመልከት


ይቻላል፡፡ ይህም የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህልና ውዝዋዜን ለመለየት፣

ለማድነቅና ለማዳበር ያስችላል፡፡ በነዚህ እንቅስቃሴዎች የተለያየ

የሰዉነት ክፍልን እናዳብራለን፡፡

75
ተግባር 1 ፡- ባህላዊ እንቅስቃሴዎች
ተማሪዎች በራሳችሁ ሙዚቃዎችን እያወጣችሁ ወይም ተከፍቶላችሁ

የተለያዩ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን በቡድን ታከናውናላችሁ


ሀ. ሙሉውን የሰዉነት ክፍል

ሙሉ የሰዉነት ክፍል ለማሟሟቅና ለማዳበር የተለያዩ ባህላዊ

እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ፡-

• የኦሮሞ፣የጉራጌና የስልጤ ማህበረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴን

…ወዘተ መስራት ትችላላችሁ፡፡


ለ. የላይኛውን የሰዉነት ክፍል

የላይኛውን የሰዉነት ክፍል ለማሟሟቅና ለማዳበር የተለያዩ

ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ፡-

• የአማራ፣የትግራይና የሃዲያ ማህበረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴን

…ወዘተ መስራት ትችላላችሁ፡፡


ሐ. የወገብና ዳሌ አካባቢ የሰዉነት ክፍል

የወገብና ዳሌ አካባቢ የሰዉነት ክፍል ለማሟሟቅና ለማዳበር

የተለያዩ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ፡-

• የወላይታ፣ የአገውና የጋሞ ማህበረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴን

…ወዘተ መስራት ትችላላችሁ፡፡

76
መ. ከወገብ በታች የሰዉነት ክፍል
ከወገብ በታች የሰዉነት ክፍል ለማሟሟቅና ለማዳበር የተለያዩ

ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ፡-


• የሐመርና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ማህበረሰብ ባህላዊ

እንቅስቃሴን …ወዘተ መስራት ትችላላችሁ፡፡


ሠ. አንድ እጅና እግር ለማሰራት

አንድ እጅና እግርን ተራ በተራ ለማሰራት የተለያዩ ባህላዊ

እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ፡-

• የአፋር ማህበረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴ… ወዘተ መጠቀም

ትችላላችሁ፡፡
ረ. ሁለት እጅ ለማሰራት
ሁለት እጅ ተራ በተራ ወደ ፊት እያሽከረከሩ ለማሰራት የተለያዩ

ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

ለምሳሌ፡-
• የሶማሌ ማህበረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴ… ወዘተ መጠቀም

ትችላላችሁ፡፡
የግምገማ ጥያቄዎች

1. በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን

መስራት ምን ጥቅም አለው?

2. እግርን የሚያሰራ ባህላዊ እንቅስቃሴን ጥቀሱ፡፡

77
6.2. በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ ጨዋታዎችን ማድነቅ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ

በኋላ፡-

• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎችን


ታደንቃላችሁ߹
• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎችን
ታሳያላችሁ߹

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄ

የሻህ ባህላዊ ጨዋታ የት ተጀመረ?

በአዲስ አበባ በርካታ ማህበረሰቦች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ማህበረሰቦች

የየራሳቸው ባህላዊ ጨዋታዎች አሉዋቸው፡፡ በዚህ ክፍል ደረጃ

የሻህ ጨዋታን ትማራላችሁ፡፡


የሻህ ጨዋታ፡- በሶማሌ ክልልና አጎራባች በሆኑ ሀረርና ድሬዳዋ
አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰብ በስፋት የሚዘወተር ባህላዊ ጨዋታ
ነው፡፡ ጨዋታው በማንኛውም የዕድሜ ክልልና ፆታ ልዩነት ሳይኖር

ይጫወታሉ፡፡ በመሆኑም ከስራ ሰዓት ውጭና በበዓላት ቀን

በማንኛውም ቦታ ሊዘወተር ይችላል፡፡ ይህ ጨዋታ የማሰብና


የአዕምሮ ብስለትን የሚያዳብር ነው፡፡
የሻህ ባህላዊ ጨዋታ በሁለት ተጫዋቾች መካከል የሚከናወን
የሰንጠረዥ ጨዋታ ነው፡፡ በዚህ ጨዋታ የመጫወቻ ቦርዱን

መካከል በማድረግ ህጉ በሚፈቅደው መሠረት የራስ ጠጠሮችን

78
በ3 ረድፍ በመደርደር የተጋጣሚን ጠጠር ከፈለጉበት በማንሳትና

እንዳይጫወት በማድረግ የመጫወቻ ቦታዎችን በመዝጋት አሸናፊ

ለመሆን የሚደረግ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡

ተግባር 1 ፡- ረ አምሳለ
የአሰራር ቅደም ተከተል
ተማሪዎች ሰዉነታችሁን ከአሟሟቃችሁ በኋላ አምስትና ከዚያ
በላይ በመሆን ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፋችሁ በተቃራኒው ከፊት
ለፊታችሁም እንደዚሁ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች
ይቆማሉ፣
ከዚያም የሚቀጥለውን ጨዋታ በተራ እየተቀባበላችሁ
ትጫወቱታላችሁ߹

• ረ አምሳለ (2 ጊዜ)

• ረ ሆይ (2 ጊዜ)

• ረ እንዴት ነሽ (2 ጊዜ)
• አለው በመከራ እንባዬን ሳዘራ
• ለምን ታዘሪያለሽ አገዳ እየበላሽ
• አገዳም የለኝ ምስኪን ደሀ ነኝ
• ምስኪን ደሀ ሆነሽ ምን በልተሽ ታድሪያለሽ
• ባገኝም በልቼ ባጣም ተደፍቼ
• እኔን ይደፋፋኝ ፆም ማደርሽ ከፋኝ
• የደጅሽ እንጆሪ አልበሰለም ወይ
• ቢበስል ባይበስል ትመጪ ይመስል
• መምጣቱንስ መጣሁ አንድ አጫዋች አጣሁ
• አንድ አጫዋችሽን ማን ወሰደብሽ

79
• አህያ ቀማኝ እግዜር በደለኝ
ተግባር 2፡- የሻህ ጨዋታ

የአሰራር ቅደም ተከተል


ሁለት ተማሪዎች ፊት ለፊት ትይዩ ተቀምጣችሁ የመጫወቻ ቦርድ
መሀል ላይ ማድረግ፣
• ጨዋታውን ለመጀመር ዕጣ ታወጣላችሁ߹
• ተወዳዳሪዎች በግላችሁ የተለያየ ቀለም ያላቸው አስራ ሁለት
ጠጠሮችን በመያዝ ተራ በተራ አንድ አንድ ጠጠሮችን
በመጫወቻ ቦርድ ላይ ትደረድራላችሁ߹
• ደርድራችሁ ከጨረሳችሁ በኃላ ቀድሞ ሦስት በመደርደር
መስመር የሰራ ካለ ጨዋታውን ይጀምራል߹
• መስመር የሰራ ከሌለ መደርደሩን ያልጀመረ ጨዋታውን
ይጀምራል߹
• ጨዋታው የሚጀመረው ጠጠር በማንሳት ነው߹

• ከዚያም ጠጠር ከማንሳት በኃላ ሦስት በመደርደር የተቃራኒን

ጠጠር በማንሳት ጨዋታው ይቀጥላል߹


• አንድ ተጫዋች ከሦስት ጠጠር በታች ከቀረው ተሸናፊ ይሆናል߹

• ሁላችሁም ተራ በተራ ተሳትፎ አድርጉ፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች

1. የሻህ ጨዋታን የትኞቹ የማህበረሰብ ክፍሎች ያዘወትሩታል?

2. የሻህ ጨዋታ ምን ጠቀሜታ አለው?

80
የምዕራፉ ማጠቃለያ

ባህላዊ እንቅስቃሴና ጨዋታ የአንድ ማህበረሰብ እሴት ነው፡፡ ይህ

እሴት በአዝጋሚ ለውጥ እየዳበረ የመጣ ሲሆን በዕረፍት ሰዓትና

በበዓላት ቀን እናከናውነዋለን፡፡ በዚህ ተሳትፎ ማድረጋችን የአካል

ብቃትን፣ መንፈሳዊ እርካታን፣ የደከም አዕምሮና የዛለ አካልን

ያበረታል፡፡ ከተለያዩ ማህበረሰቦች ጋር ባህላዊ እንቅስቃሴ ላይ

ተሳትፎ ማድረግ ቋንቋን፣ ባህልንና ውዝዋዜን እንድናዳብር


ይረዳናል፡፡ የሻህ ጨዋታ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የሚዘወተርና

በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ተሳትፎ ያደርጉበታል፡፡

81
የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች

ሀ. እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ፡፡

1. ባህላዊ እንቅስቃሴ የአንድ ሀገር እሴት ነው፡፡

2. ባህላዊ እንቅስቃሴዎች ከአካባቢ አካባቢ ልዩነት የላቸውም፡፡

3. ባህላዊ ጨዋታዎችን ማከናወን አካልን ያዳብራል፡፡

4. የሻህ ባህላዊ ጨዋታ በሁለት ተጫዋቾች መካከል

ይከናወናል፡፡

5. ባህላዊ ጨዋታዎችን በበዓላት ቀን ብቻ እንጫወታለን፡፡

ለ. ትክክኛውን መልስ ምረጡ

6. የሻህ ጨዋታ በማን ሊዘወተር ይችላል፡፡

ሀ. በወንዶች ለ. በሴቶች ሐ. ሁሉም

7. ባህላዊ እንቅስቃሴና ጨዋታ ላይ መሳተፍ ምን ጠቀሜታ

አለው?

ሀ. ለአካላዊ ብቃት ለ. የመንፈስ መረበሽ ሐ. መልስ

የለም
8. ባህላዊ ጨዋታ እንዴት ልናከናውን እንችላለን?

ሀ. በግል ለ. በቡድን ሐ. ሁሉም

82
የቁልፍ ቃላት ፍቺ

መንደር- በርከት ያለ ህዝብ የሚኖሩበት አካባቢ


መጋጠሚያ- መገናኛ፣መያያዣ ቦታ
ማህበረሰብ- በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች

ማህበራዊ - በህብረት፣ በጋራ፣ በትብብር የሚከናወን ተግባር


ነው፡፡
ሸብረክ- ከጉልበትመታጠፍ
ቅምብቢት- ከታች ሰፋ ብሎ ከአናቱ ጠበብ ያለ ቅርፅ ያለው ቁስ
ብርታት- ፅናት መኖርን የሚያሳይ ነው፡፡
ብቃት- አንድን ነገር የማከናወን አቅም
ተዳፋት- ዝቅ ያለ ቦታ
ተጨባጭ- የተረጋገጠ߹ የታወቀ߹ ማስረጃ ያለው߹ የሚዳሰስ እና
በስሜት የሚገለፅ ነው፡፡
ኃይል- ከምንመገበው ምግብ የምናገኘውና የየዕለት ሥራችንን
በብቃት እንድንወጣ የሚያደርግ አቅም ነው፡፡
እሴት- ዋጋ ያለው ነገር፣ አስፈላጊ ነገር፣ ጠቃሚ
ክህሎት- በስልጠና የሚገኝና አንድን ተግባር በአግባቡ መስራት
የሚያስችል ችሎታ ነው፡፡
ዑደት- ዙሪያ፣ ተመሳሳይ መነሻና መድረሻ ያለው

ድጋፍ- ምርኩዝ ፣ረዳት

ጫና- ቀድሞ ከነበረው አቅም በላይ የሚጠይቅ ተግባር

83
ዋቢ መጽሐፍት
➢ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ( 2009 ዓ.ም) የሥነጥበብና

ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሀፍ

➢ ማስትር ንጉሴ ጎቻለው (2010 ዓ.ም) አደገኝና ጎጂ ስፖርታዊ

እነቅስቃሴዎች ከነምቹ አማራጮቹ

➢ ማስተር ወንድሙ በልሁ (2002 ዓ.ም) የአካል ብቃት

እንቅስቃሴ ለተስተካከለ የሰዉነት ቅርፅ ለወንዶችና ለሴቶች

➢ የትምህርት መሣሪያዎች ማደራጃና ማከፋፈያ ድርጅት

(1970ዓ.ም) የመተጣጠፍ መገለባበጥ ከ1-12 ክፍል

የመምህሩ መምሪያ
➢ የትምህርት መሣሪያዎች ማደራጃና ማከፋፈያ ድርጅት

(1971 ዓ.ም) የመሣሪያ ጅምናስቲክ ትምህርት የመምህሩ

መምሪያ 1ኛ-12ኛ ከፍል

➢ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌደሬሽን


➢ ከስርዐተ ትምህርትና ሱፐርቪዥን መምሪያ የተዘጋጀ (1968

ዓ.ም) ልዩ ልዩ ጨዋታዎች ከ 1ኛ-12ኛ ክፍል የመምህሩ


መምሪያ

84
➢ w.w.w. youthuble.com/Watch
➢ w.w.w. youthuble.com/results
➢ Social Awarenes. /httpsi//transforming
education.org>Resource
➢ Self Management /httpsi//w.w.w.betterup.com
➢ Social Relationsheip /httpsi//w.w.w link

springer.com

85
104

86

You might also like